ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለመስቀል ደመራ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሰተላለፉ
ሀዋሳ፡ መስከረም 16/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዓሉን በፍቅርና በአብሮነት፣ በመረዳዳትና በመተጋገዝ፣ አቅመ ደካማ ወገኖቻችንንና አረጋዊያንን በመደገፍ በጎ ተግባራትን አየፈፀምን ማከበር እንደሚያስፈልግ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁም ብለዋል።
መስቀል አምላክ ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅሩን የገለፀበት፤ ይቅርታንና የኃጢያት ስርየትን ለሰው ልጆች የሰጠበት መለኮታዊ አንድምታ ያለው ሲሆን በመስቀል ፍቅር፣ ሰላም፣ ይቅርታና መተሳሰብ የሚገለፅበት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር የኢትዮጵያዊነታችን ማድመቂያ የእርስ በርስ መዋደዳችን መገለጫ መሆን ይገባል።
የመስቀልን ደመራ በዓል አከባበር ህዝብ በጋራና በአብሮነት በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ማክበር አንዱ የኃይማኖታዊ ሥርዓቱ ሲሆን በአደባባይ ከኃይማኖታዊ ክዋኔ ባሻገር ለሀገሪቱ ትልቅ የቱሪዝም ሀብት ሆነዋል። ይህንን ዕንቁ በዓል የበዓል እሴቱ በጠበቀ መልክ በማክበርና ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ትልቅ ቤት ሥራችን ነው ብለዋል።
ከበርካታ ሀገራት በዓሉን ለመታደምና ቱሪስቶች ወደ ሀገሪቱ ስለሚመጡ የተለመደውን ኢትዮጵያዊ ጨዋነታችንንና እንግዳ ተቀባይነታችንን ልናሳያቸው ይገባል ብለዋል።
ምንጭ፡ የሲዳማ ብ/ክ/መ/ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ