በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ባውዲ በክልሉ የሚገኙ የየተለያዩ ብሔሮች ዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ !!
የመልዕክቱ ሙሉ ሃሳብም እንደሚከተለው ይቀርባል ፡፡
በክልላችን የሚገኙ የወላይታ (ዮዮ-ጊፋታ)፣ የጋሞ (ዮ- ማስቃላ)፣ የጎፋ (ጋዜ ማስቃላ) እና የኦይዳ (ዮኣ – ማስቃላ) ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓል የአዲስ ዓመት መሻገሪያ ብስራት የሚበሰርበት እና የምስጋና በዓላት ናቸው።
ክልላችን የብዝሃ ባህል እና ታሪክ፤ የቋንቋዎች እና እምነቶች፣ የመልካም እሴቶች፣ ዎጎች፣ ልማዶች እና የውብ ተፈጥሯዊ መስህቦች የያዘች ትንሿ ኢትዮጵያ በመባል ትታወቃለች። እነዚህን የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ባህሎችንና ፀጋዎች ከነሙሉ ክቡብራቸው ሞገሳቸው ጠብቆ ለትዉልድ ለማስተላለፍ ፓርቲያችን አቅዶ እየሰራ ይገኛል።
በክልላችን የሚገኙ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላት ቱሪዝም ኢንዱስትሪና ለአገሪቱ ኢኮኖሚም ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ይታወቃል።
በዓላቱ በህዝቦች መካከል አብሮነትን፣ አንድነትን፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ይበልጥ እንዲጠናከር እንደሚያግዝና ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ እምርታ የሚያበረክተው አስተዋጽኦም እጅግ የጎላ መሆኑ እሙን ነው።
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የክልላችን ህዝቦች አዲሱ ክልላችን ሠላሙ የሰፈነበት፣ ፍቅር የሚጎለብትበት፣ ፍትህ የሚሰፍንበት፣ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚረጋገጥበት፣ አብሮነትና ወንድማማችነት የሚጸናበት፣ መተሳሰብና መደጋገፍ የሚታይበት እና ኢትዮጵያዊነት የሚጸናበት እንዲሆን ሁላችሁም የበኩላችሁን አሻራ እንድታበረክቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
ወንድማማችነትና እህትማማችነት ዕሴት ባለበት ሁሉ መረዳዳት አለ፤ ብልጽግና ፓርቲ ወንድማማችነትንና እህትማማችነት ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ ሲነሳ የሁሉም ችግሮች ማሰሪያ ውል እንደሆነ ስለሚያምን ነው፡፡ ስለዚህ የዘመን መለወጫ በዓላቱን ስናከብር የተለመደውን ኢትዮጵያዊነት እንድታሳዩ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
በዓሉን ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በመደጋገፍ፣ በመጠያየቅና በፍቅር የሚያከብሩት እንዲሁም የሠላም፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ፣ የመቻቻልና አንድነታችንን የሚናጠናክርበት እንዲሆን ልባዊ ምኞቴ ነው።
በሀገራችን የተጀመረው የለውጥ ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ብልጽግና ፓርቲ የጀመራቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ውጥኖችን ከግብ ለማድረስ ሁላችንም በተሰማራንበት መስክ ጠንክረን መስራት ከቻልን የምንመኘውን ሁለንተናዊ ብልጽግናን በቅርቡ እውን ማድረግ እንችላለን።
ዮዮ-ጊፋታ!
ዮ- ማስቃላ!
ጋዜ ማስቃላ!
ዮኣ – ማስቃላ!
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ