የካፈቾ ብሄር ዘመን መለወጫ በዓል ያለ ምንም የትራፊክ አደጋ እንዲጠናቀቅ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የካፋ ዞን ትራስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ
ሀዋሳ፡ መስከረም 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የካፈቾ ብሄር ዘመን መለወጫ በዓል ያለ ምንም የትራፊክ አደጋ እንዲጠናቀቅ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የካፋ ዞን ትራስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አስታውቋል፡፡
በዓሉን ለማክበር ለሚመጡ ሰዎች የማጓጓዣ እጥረት እንዳይኖር ዝግጅት መደረጉን መምሪያው ገልጿል፡፡
በቦንጋ ከተማ ቦንጌ ሻምበቶ በሚጓጓዙበት ወቅት በቂ የትራንስፖርት አቅርቦት እንዲኖር ከወረዳ እና ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ነው የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ዘመዴ አንዳርጌ የገለፁት፡፡
ከወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚነሱ የበዓሉ ተሳታፊዎች ያለ ምንም የትራንስፖርት እጥረት በዓሉን እክብረው ወደየመጡበት እንዲመለሱ ግብረ-ሃይል በማቋቋም እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ዘመዴ ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡
ከባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች እንዲሁም ከትራንስፖርት ማህበራት ጋር በመነጋገር የትራንስፖርት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን ይህንን ሁሉም የሚመለከተው አካል ገቢራዊ እንዲያደርግ የመምሪያው ሃላፊ ጠይቀዋል፡፡
በየወረዳዎች የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ከትራፊክ ፖሊሲች ጋር በመናነበብ ምንም አይነት የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰትም የቅድመ ጥንቃቄ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
ብሔራዊ የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ መያዝ የተሻለ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚጠቅም ተገለጸ
በክልሉ በ2018 በጀት አመት ከ336 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ከምዝበራና ከብክነት ማዳን መቻሉ ተገለጸ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ከ45.7 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ