የትምህርት ጥራት ለማምጣት በሚከናወን ተግባር ላይ ሁሉም አካላት አበክረው መስራት እንዳለባቸው ተመላከተ
ሀዋሳ፡ መስከረም 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የትምህርት ጥራት ለማምጣት በሚከናወን ተግባር ላይ ሁሉም አካላት አበክረው መስራት እንዳለባቸው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
ቢሮው ለዞን፣ ወረዳ፣ ትምህርት ቤት አመራር እና መምህራን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዲሱ ስርአተ ትምርት ትገባራ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ መድረክ አካሂዷል።
ከትምህርት ጥራት ችግር ጋር ተያይዞ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ አዲስ የትምህርት ፖሊስ ተዘጋጆቶ ወደ ስራ ተገብቷል።
አዲሱን የትምህርት ፖሊስን መሠረት በማድረግ በሙከራ ደረጃ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ሲተገበረ የነበረው የትምህርት አሰጣጥ በዘተያው አመት ወደ ሙሉ ትግበራ ይገባል።
በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአዲሱ ስርአተ ትምህርት ትግበራና የመፅሀፍ ትውውቅ መድረክ ላይ የተገኙት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ማርቆስ ቡልቻ፤ አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ በጥሩ ስነ-ምግባር የተነፀ ዜጋ በማፍራት በኩል እና የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰው ሁሉም አካላት አበክሮ መንቀሳቀስ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በተያዘው አመት በአዲሱ ፖሊሲ ሙሉ በሙሉ ወደ ትገባራ የሚገባው የ2ኛ ደረጀ ትምህርት ከመምህራን ጀምሮ የትምህርት አመራሮች ሙሉ ግንዛቤ ይዘው ወደ ስራ እንዲገቡ ለማስቻል የተዘጋጀ መድረክ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የቤንች -ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ግዛው ሀይሌ በበኩላቸው አዲሱን የትምህርት ፖሊሲ መሠረት በማድረግ የሙከራ ትግበራ ሲደረግ እንደነበረ አመልክተው በሙከራ ተግበራ ወቅት የተገኙ ውጤቶች ለሙሉ ትገበራው አቅም እንደሚፈጥሩም አመላክተዋል።
በግንዛቤው መድረክ ላይ የአዲስ ትምህርት ፖሊሲ በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርቱ አተገባበር ላይ ያተኮረ ግንዛቤ ከመሠጠቱ ባለፈ የመፀሐፍ ትውውቅ ተደርጓል።
የሸካ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ መስፍን አለሙ እና የምዕራብ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ አበቃ ፈለቀ፤ በየዞናቸው በሙከራ ትግበራ ወቅት የተለያዩ ስራዎች ሲሠሩ መቆየታቸውን አመልክተው ችግሮችን በመለየት መፍትሔ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር አንስተዋል።
በሚዛን አማን ከተማ በተካሄደው መድረክ ላይ የሸካ የምዕራብ እና የቤንች ሸኮ ዞን የትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።
ዘጋቢ፡ ብዙአየሁ አሣሣኸኝ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ