በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን የጂንካ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 7ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አካሄደ
ሀዋሳ፡ መስከረም 08/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን የጂንካ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 7ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አካሄዷል።
ምክር ቤቱ በአሪ ዞን ዋና አስተዳደሪ በአቶ አብርሃም አታ በኩል የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አስፋው ዶሬን ዕጩ አድርገው አቅርበው በምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።
በተመሳሳይ ወ/ሮ አንለይ እርገጤ የጂንካ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ሆነው እንዲያገለግሉ የጂንካ ከተማ ከንቲባ አቶ አስፋው ዶሬ አቅርበው በምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።
በተጨማሪ ከንቲባው አቶ ማንጎ ከበደን በአሪ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ረዳት የመንግስት ተጠሪና ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የሪዮተዓለም ዘርፍ ሀላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ቀርቦ በምክር ቤቱ ሙሉ ይሁንታን አግኝቷል።
የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ባደረጉት ንግግር ከተማው የሁሉም ኢትዮጵያን በመሆኑ በጋራ አንድነትና ለለውጥ ተግተን ልንሠራ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ብዙ መልማትና መጠቀም የሚገባን የኢኮኖሚ አውታሮች በመኖራቸው በሰከነ መልኩ አንድነታችንን አጠናክረን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሠራለን ሲሉም አቶ አብርሃም አታ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አዲስ የተሾሙት የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አስፋው ዶሬ በበኩላቸው የህዝቦች አንድነትና ሠላም ተረጋግጦ የተሻለ ልማትና ዕድገት በከተማው እንዲመዘገብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።
ምክር ቤቱም በቀረበው ሹመት አጀንዳ ዙሪያ በመምከር አስቸኳይ ጉባኤውን አጠናቋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ