ተላለፊና ድንገተኛ ወረርሽኝ በሽታዎችን ለመግታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ምክክር በጂንካ ከተማ ተካሔደ
ሀዋሳ፡ መስከረም 08/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ድንገተኛ አደጋዎች ኦፕሬሽን ማዕከል ተላለፊና ድንገተኛ ወረርሽኝ በሽታዎች ዙሪያ የጋራ ምክክር በጂንካ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በጂንካ ከተማ ከተደራጁ የማህበራዊ ክላስተር ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ አንዱ ሲሆን ተቋማቱ ወደ ሥራ መግባታቸውን ተከትሎ፥ የድንገተኛ አደጋዎች ኦፕሬሽን ክላስተሩ ከተደራጀ በኋላ የመጀመሪያ የሆነውን ውይይት እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የልማት አጋር ድርጅቶች፣ የማዕከሉ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ታዬን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተው በ36 ሳምንታት አፈፃፀም ዙሪያ እየመከሩ ነው።
ወባ፣ ኮሌራ የምግብ እጥረት እና በሌሎችም በወረርሽኝ መልክ ሊገለፁ በሚችሉ በሽታዎች ዙሪያ ሪፖርት ቀርቦ ምክክር እየተደረገበት ነው።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ