የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የሰላም እሴት ግንባታ ተግባራትን ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳደር ገለፀ
ሀዋሳ፡ መስከረም 07/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የሰላም እሴት ግንባታን ተግባራት ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳደር ገልጿል፡፡
የቤንች ሸኮ እና የምዕራብ ኦሞ ዞኖች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚያስችል የጋራ የምክክር ፕሮግራም በጎሪ ጌሻ ከተማ አካሂደዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ጌታቸው ኬኒ እንደገለፁት፤ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የሰላም ዕሴት ግንባታ ተግባራትን ቀጣይነት ማረጋገጥ ይገባል።
የወንድማችነትን ግንኙትን ማጠናከር በዞኑ እና አጐራባች ዞኖች አካባቢ ለተጀመሩ የልማት እና መልካም አስተዳደር ተግባራት መሳካት ፋይዳው የጐላ እንደሆነ ዋና አስተዳደሪው ገልፀዋል፡፡
በተለይም በቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ለተጀመረው የሠላምና ፀጥታ ተግባራት መሳካት የህዘብ ለህዘብ ግንኙነት መጠናከር ድርሻው የጐላ በመሆኑ በዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት አቶ ጌታቸው አስረድተዋል፡፡
የቤንች ሸኮ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኮጁ ባዳካች በበኩላቸው ሠላም ለልማትና መልካም አስተዳደር እሴት ግንባታ ተግባራት መሳካት ያለው ሚና የላቀ በመሆኑ ለዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ በሁለቱም ዞኖች መካከል ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
በተለይም የቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞን ህዝቦች ሠላማቸው ተጠብቆ በደስታና ሀዘን ጊዜ የሚገናኙበትን የወንድማማቾችን ግንኙነትን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
በምዕራብ ኦሞ ዞን የጐሪጌሻ እና በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ አስተዳዳሪዎች በሁለቱም ዞኖች የሚገኙት ህዝቦች በጋብቻ እና በባህል የተሳሰሩ መሆናቸውን ገልፀው የወንድምማማች ህዝቦች ግንኙነት ለማጠናከር በመንገድ መሠረተ ልማት ድልድይ ግንባታ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡
የሁለቱም ዞን ሕዝቦች ቱባ ባህልንና እሴትን ለማጠናከር በቀጣይ በቅንጅት እንደሚሰራም ተጠቁሟል።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ አሰፋ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ