የፓን አፍሪካ የወባ ትንኝ ቁጥጥር 9ኛ ኮንፍራንስና አውደ ርእይ በአዲስአበባ እየተካሄደ ነው
በኮንፍረንሱ ለይ ከ36 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች ተሳትፈውበታል ።
በኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ህይወት ሰለሞን እንደገለጹት የወባ በሽታ በአፍሪካ 95 ከመቶ በላይ ሞትና ህመም ያስከትላል ።
ኢትዮጵያ የወባ በሽታን የመከላከሉን ሥራ ከ60 ዓመታት በላይ ስትሠራ መቆየቷንም ተመላክቷል ።
በ2015 ዓ/ም ብቻ ከ19.5 ሚሊዬን በላይ የአልጋ አጎበሮችን ማሰራጨት የተቻለ ሲሆን በተለያዩ አከባቢዎች የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት መካሄዱንም ዶክተር ህይወት አስረድተዋል ።
በኮንፍረንሱ ላይ የሚቀርቡ ጥናቶች በቀጣይ የወባን ስርጭት የመከላከሉን ሥራ በኢትዮጵያ ቢሎም በአፍሪካ አህጉር አጠናክሮ ለመቀጠል አጋዥ ግብአት ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም መሪ ሥራ አሰፈጻሚዋ ገልጻለች ።
በኮንፍራሱ በአፍሪካ በአዲስ መልክ በገባችው የወባ አስተላለፊ ትንኝ ዙሪያም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች የሚሠሩበት እንደሚሆን ተጠቁሟል ።
በ9ኛው የፓን አፍሪካ የወባ ትንኝ ቁጥጥር ጉባኤ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮችም ተሳትፈዋል ።
በአዲስአበባ ስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄ ያለው ዓመታዊ ኮንፍረንሱ እስከ ፊታችን አረብ የሚቀጥል እንደሆነም ታውቋል።
ዘጋቢ ፡ ጌታሁን አንጭሶ

More Stories
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም #ደሬቴድ – ቀጥታ ስርጭት #ዜና24 #ዜና #ደቡብቴቪ
የልማት ሥራዎችን ለማሣካት የሚመደብ በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የጋራ ርብርብ እንደሚጠይቅ ተመላከተ
ሴቶች የቁጠባን ባህል በማዳበር የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግ በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ