ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን በማፍራት ረገድ የግል ትምህርት ተቋማት አስተዋጸኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን በማፍራት ረገድ የግል ትምህርት ተቋማት አስተዋጸኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ መስከረም 05/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን በማፍራት ረገድ የግል ትምህርት ተቋማት  አስተዋጸኦ ከፍተኛ መሆኑን  የሸኮ ወረዳ ዋና አስተዳደር አስታወቀ።

የአብሲንያ ሻይን ቢዝነስ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በሽኮ ካምፓስ  ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4 ያሰለጠናቸውን 155 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 74ቱ ሴቶች ናቸው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ንግግር  ያደረጉት የኮሌጁ ባለቤት አቶ አስራት አበበ ከአከባቢው ራቅ ባለ ቦታ ይማሩ የነበሩ የአከባቢው ልጆች በአቅራቢያቸው የትምህርት እድል ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም የበለጠ የአከባቢውን ፍላጉት መነሻ ባደረጉ መልኩ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ኮሌጁ እንደሚያሰለጥን ተናግረዋል፡፡

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ  አቶ አሪ ጉርሙ በበኩሏቸው ለኮሌጁ ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትያስተላለሁ ሲሆን ኮሌጁ የአከባቢውን ወጣቶ በማስልጠን የስራ እድል እንዲፈጥሩ በማስቻል ረገድ አጋዥ በመሆኑ ለኮሌጁ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ገበየሁ ብዙአየሁ- ከሚዛን ጣቢያችን