ጊፋታ የሠላም፣ የእርቅ፣ የመቻቻልና የአብሮነት በዓል በመሆኑ በመረዳዳት ማክበር እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡መስከረም 05/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ጊፋታ የሠላም፣ የእርቅ፣ የመቻቻልና የአብሮነት በዓል እንደ መሆኑ በመረዳዳት ማክበር እንደሚገባ በየወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ገለጸ፡፡
“አዲሱ ትውልድ የጊፋታ በዓል ያከብራል” በሚል መሪ ቃል በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ከወጣቱ ክፍል ጋር ውይይት ተደርጓል::
የውይይት መድረኩ ወጣቱ ትውልድ የጊፋታን በዓል ከመቼውም ጊዜ በላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ማክበር እንዳለበት የሚያስችል መሆኑን የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ አይዛ ተናግረዋል፡፡
“ጊፋታ” የሠላም፣ የእርቅ፣ የመቻቻል፣ የአብሮነትና የፍቅር በዓል በመሆኑ በዓሉን በመረዳዳትና አቅም የሌላቸውን በማገዝ ማክበር እንደሚባም ተገልጿል፡፡
ወጣት በረከት ማደቦ፣ ወጣት ፀጋነሽ ኢሳያስ እና ወጣት ከተማ ፋንታ የውይይቱ ተሳታፊዎች ሲሆኑ “ጊፋታ” በዓል ባህላዊ ይዘቱን ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል::
የ”ጊፋታ”ን በዓል ለማክበር በርካታ እንግዶች ወደ ከተማችን ስለሚመጡ የውበት ስራዎችን ጨምሮ በተለያዩ ተግባራት ለይ እየተሳተፈን እንገኛለን ያሉ የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች እንግዶችን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል::
አዘጋጅ: ተስፋሁን ሳርካ – ከዋካ ቅርንጫፍ
More Stories
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ