ይቅርታ ካገኙ ታራሚዎች መካከል 12ቱ ሴቶች ናቸው።
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ እና የክልሉ የይቅርታ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ማቶ ማሩ እንደገለፁት የክልሉ ርዕሰ መስተደድር የኢትዮጵያውያን አዲስ አመት መግባት ምክንያት በማድረግ ለታራሚዎቹ ይቅርታ መስጠታቸውን ተናግረዋል።
ታራሚዎቹ የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ወደ ማረሚያ ተቋማት መግባታቸውን ጠቅሰው በቆይታቸውም መልካም ስነ ምግባር ያሳዩ እንደሆኑም አስረድተዋል።
በይቅርታ የተለቀቁ ታራሚዎች የበደሉትን ህብረተሰብ እና መንግስት እንዲክሱ በአንፃሩ ደግሞ ህብረተሰቡም ታራሚዎችን ተቀብሎ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል የፍትህ ቢሮ ሀላፊው።
ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/