የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ወቅት የቀድሞው ደቡብ ኦሞ ዞን ሁለት ዞኖች ሆኖ እንዲደራጅ በተወሰነው መሰረት ሁለቱ ዞኖች ነገ በይፋ እንደሚደራጁ ተገለፀ
ከዚህ በፊት ደቡብ ኦሞ ዞን 10 ወረዳዎችና 3 ከተማ አስተዳደሮች በአንድ ላይ ተደራጅተው ልማታዊ ሥራዎችን እያካሄዱ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን በቅርቡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ወቅት ዞኑ ሁለት ዞኖች ሆኖ እንዲደራጅ መወሰኑ የሚታወስ ነው።
በዚህም ሐመር፣ ማሌ፣ ሳላማጎ፣ ዳሰነች፣ ኛንጋቶምና በናፀማይ ወረዳዎች እና ቱርሚ ከተማ አስተዳደር በአንድ ላይ የሚደራጁ ሲሆን በሌላ በኩል ሰሜን፣ ደቡብ፣ ዎባ እና ባካ ዳውላ አሪ ወረዳዎች በተጨማሪ ገሊላና ጂንካ ከተማ አስተዳደሮች በአንድ ላይ ዞን እንደሚመሠረቱ መገለፁ የሚታወስ ነው።
ሁለቱም ዞኖች ነገ ጳጉሜ 06/2015 ዓ.ም በይፋ እንደሚደራጁ ታውቋል።
ምሥረታው የተሳካ እንዲሆን በሁለቱም በኩል በኮሚቴ እየተሠራ ሲሆን በናፀማይ፣ ማሌ፣ ሐመር፣ ዳሰነች፣ ኛንጋቶ፣ ሳላማጎ እና ቱርሚ ከተማ አስተዳድሮች በአንድ ላይ በሚያደራጀው የምስረታው ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ተመስገን ጋርሾ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ