በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወልቂጤ ከተማ የመንግስት ተቋማት ስራ በይፋ ተጀመረ
ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 04/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወልቂጤ ከተማ የመንግስት ተቋማት ስራ በይፋ ተጀምሯል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎ፣ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ዘረፍ አስተባባሪና የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መሀመድ ኑሪዬ ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በይፋ ስራ ጀምሯል።
የኢትዮጵያ ሰንድቅ አለማ እና የክልሉ ሰንደቅ አለማ የመስቀል መርሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ የክልሉ ስራ ሀላፊዎች የቢሮ ርክክብና ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በዛሬ ዕለት ስራ በወልቂጤ ከተማ የጀመረው መንግስት ተቋማት ህግ አውጭና የመስረተ ልማት ክላስተር ቢሮ መገኛ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።
ዘጋቢ: ፋሲል ሀይሉ
More Stories
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ