ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 02/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ጀግና ህዝብና ትውልድ መፍጠር እንደሚቻል ታሪክን ካቆዩልን አያቶች በመማርና የከፈሉትን መስዋዕትነት በመዘከር ሀገርን ማፅናት እንደሚገባ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡
ጳጉሜን 2 የሚከበረውን የመስዋዕትነት ቀን ምክንያት በማድረግ አስተያየታቸውን ከሰጡት የወላይታ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ወ/ሮ ፍሬህይወት ደመቀ፣ አቶ ምስጋናው አየለ፣ ወ/ሮ ምህረት አድማሱ እና ተመስገን አደለ፤ ኢትዮጵያ ይህን የመስዋዕትነት ቀን የምታከብረው ያሳለፈችው አኩሪ ታሪክ ስላላት ነው ያሉት ነዋሪዎቹ ታሪክን ለትውልድ ከማሻገር አንፃር ትውልዱም ሀገሩን ጠብቆ ለማቆየት የዛሬዋን ኢትዮጵያ ትናንት መስዋዕትነት ከፍለው ያቆዩን አርበኛ አያቶች ማሰብና መዘከር ይገባል ብለዋል፡፡
ወጣቱ ትውልድ በተሰማራበት ዘርፍ ጥንካሬና ታታሪነቱን በማጠናከር ለሀገሩ ሊከፍለው የሚገባውን መስዕዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ሊሆን እንደሚገባና ለመጭው ትውልድም መልካም ታሪክን ፅፎ ማቆየት እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ትዉልዱ የተጣለበትን ኃላፊነት በታማኝነት በመወጣትም ሀገርን ከሚያፈርሱ ተግባራት በመጠበቅ በመስዋዕትነት የተገኘዉን አንድነት ማስቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።
መስዋዕትነት የራስን ህይወት አሳልፎ የሚሰጥ ትልቅ ስጦታ በመሆኑ ለሀገሪቷ መስዕዋትነት የከፈሉ አያቶቻችን ወደፊትም አሁንም እየከፈሉ ላሉ አካላት ከጎናቸው በመቆም እንደሚደግፉና የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ “በመስዋዕትነት የምትፀና ሀገር” በሚል የሚከበረውን ጳጉሜን 2 የመስዋዕትነት ቀን ዕለት ለሀገራቸው መስዋዕትነት ከፍለው ያለፉ አያቶችን በመዘከርና በማሰብ እያከበሩ መሆናቸውን ነው ነዋሪዎቹ የገለፁት፡፡
ዘጋቢ፡ ብዙነሽ ዘውዱ
More Stories
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ