በደም የተከበረች ሀገርን ዛሬም በላባችን ሁላችንም ዜጎቿ ልንቆምላት ይገባል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ

በደም የተከበረች ሀገርን ዛሬም በላባችን ሁላችንም ዜጎቿ ልንቆምላት ይገባል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ

ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 02/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደም የተከበረች ሀገርን ዛሬም በላባችን ሁላችንም ዜጎቿ ልንቆምላት ይገባል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ ገለፁ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የፀጥታ አካላት ለሀገራቸው ዋጋ ከፍለው ያለፋ ጀግኖችን በማሰብ አክብረዋል።

ዕለቱንም በመስዋእትነት የምትፀና ሃገር!” በሚል የሚከበረውን ጷጉሜ 2 ምክንያት በማድረግ ሰነድ ቀርቦ የፖናል ዉይይት ተደርጓል።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ እንዳሉት በደም የተከበረች ሀገርን ዛሬም በላባችን ሁላችንም ዜጎቿ ልንቆምላት ይገባል።

ከራሱ በላይ ሀገሩን ወዶ ደሙን ከፍሎ አካሉን ሰጥቶ ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ለሚያደረጉ የሠላም አስጠባቂ አካላት ጀግና ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ በመስዋዕትነት ትፀናለች በሚል ዕለቱን በማመስገንና በማሰብ እናከብራለን ሲሉ ገልጸዋል።

ለሀገራቸን የመከላከያ ሠራዊት፣ የሠላምና ደህንነት ተቋማት ለሀገራቸዉ ለሚከፍሉት መስዕዋትነት የክልሉ መንግስት ከፍ ያለ ክብር ምስጋና እንዲሁም እውቅና ያቀርባል ነው ያሉት ኃላፊው።

የሠራዊት አካላት ቤተሰብን በመጎብኘት በመጠየቅና እገዛ በማድረግ ሁሉም አካላት ከጎናቸው መቆም እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

በክልሉ ያሉ የፀጥታ ኃይሎችም በአዲስ ዓመት አዲስ በተመሠረዉ ክልል የሚጠየቁ ተልዕኮዎችን በኃላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የወላይታ ዞን መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጎአ በበኩላቸው ጥንት አርበኛ አያቶች የሀይማኖት የዘር ብዝሃነት ሳይገድባቸዉ በከፈሉት መስዕዋትነት ልናከብራቸው ልናሳስባቸው ይገባል ነው ያሉት።

መስዕዋትነት ማለት ዜጎች ለራሳቸው ለነፍሳቸው ሳይሰስቱ ሀገራቸውን በፅናት አስጠብቀው የሚጠብቁበት ነው ያሉት በመድረኩ የተሳተፋ የዞኑ ፖሊስ አባላቶች ለሀገራችን መስዕዋትነት ከፍለው ያቆዩልንን አያቶች በማሰብ እኛም ሀገራችንን በማስጠበቅ ለትዉልድ እናቆያለን ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

መጪው ዓመት የሰላም የአብሮነት የፍቅር እንዲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ መልካም ምኞተታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ፡ ብዙነሽ ዘውዱ