የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ባዕድ ነገሮችን በመቀላቀል የሚሸጡና ሐሰተኛ የብር ኖቶችን የሚያዘዋዉሩ ሰዎችን ሕብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት እንዲያሳዉቅ የጂንከ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ጥሪ አቀረበ
ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 02/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ባዕድ ነገሮችን በመቀላቀል የሚሸጡና ሐሰተኛ የብር ኖቶችን የሚያዘዋዉሩ ግለሰቦችን ሕብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ የጂንከ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡
የከተማዉ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሽብሩ አማረ እንደገለጹት መጪዉን አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ አርሶና አርብቶ አደሩ በጥራት ያፈራቸዉን ንብረቶች ወደ ገበያ በሚያቀርቡበት ወቅት በሀሰተኛ የብር ኖቶች አዘዋዋሪ ሕገ- ወጥ ነጋዴዎች እንዳይታለሉ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነዉ ብለዋል፡፡
ከበአል ግብይት ጋር ተያይዞ ባዕድ ነገሮችን በመቀላቀል በርካሽ ዋጋ የሚያቀርቡ ስግብግብ ነጋዴዎች ስለሚኖሩ ሸማቾች ሲገበያዩ በጥራት ዙርያ ትኩረት በማድረግ ማረጋገጥ እንዳለባቸዉም ፖሊስ አዛዡ አሳስበዋል፡፡
ከዚህ በፊት ከ18 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ሲያዘዋዉሩ በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች መኖራቸዉም በመግለፅ፡፡
ፖሊስ አዛዡ አያይዘዉም መጪዉን የአዲስ ዓመት በማስመልክት የሚፈፀሙ ወንጀሎችና ሕገ- ወጥ ስግብግብ ነጋዴዎችን በማጋለጥ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲተባበር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ሁሴን አለሙ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ