እንኳን ለጳጉሜን 1 የአገልጋይነት ቀን አደረሳችሁ! – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ዛሬ ጳጉሜን 1 ነው፤ የአገልጋይነት ቀን፡፡ ማገልገል ክብር ነው፣ እንደ ኢትዮጵያ በበዙ ተስፋና ፈተና ያለች ሀገርን ማገልግል ደግም ድርብ ክብር ነው፡፡
በመላው ሀገራችን የዛሬውን ቀን ስናክብር ለሀገራችን በየተሰማራንበት ዘርፍ ውጤታማ የሆነ አገልግሎት በመስጠት የራሳችንን አሻራ እያሳረፍን መሆናችንን በማመን ሊሆን ይገባል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ የመንግስት ሰራተኞች አሏት፣ ይሄ ቁጥር ቀላል የማይባሉ ሀገራት የህዝብ ቁጥር ነው፡፡
የአገልግሎት አሰጣጣችንን በማሻሻል በቁጥራችን ልክ የሚገባንን ሀላፊነት ከተወጣን በብዙ መልኩ ለነገው ትውልድ መንገድ በመጥረግ ጉልህ አሻራችንን እያስቀምጥን መሆኑን ልንጠራጠር አይገባም፡፡
የሀገራችን ልማት እና ቀጣይ እድገት ብሎም የሰላም መሰረት አገልገሎት አሰጣጣችን ያለው ሚና በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ የኢኮኖሚ እድገቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ፈጣን የሆነ አገልግሎት መስጠት የግድ መሆኑን ለአፍታም ቢሆን ልንርሳው የማይግባ ጉዳይ ነው፡፡
የሀገራችን ኢኮኖሚ በብዙ ውስጣዊ እና አለም አቀፋዊ ፈተናዎች እየተፈተነ በአለም በፈጣን እድገት ላይ ካሉ ሀገራት ተርታ የሚመደብ ነው፡፡
በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች በቀጣይ ሙሉ ፍሬ እንዲያፈሩ የአገልገሎት አሰጣጥ ማሻሻያወች እና የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሞ ተግባራት በመንግስት በኩል እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
እነዚህ ጅምር የለውጥ ተግባራት በሙሉ ፍሬ ለህዝቡ ደርሰው ዘላቂ ችግሩ እንዲፈታ እኔ በተሰማራሁበት መስክ፣ በያዝኩት የስራ መደብ የሚጠበቅብኝን ሀላፊነት እየተወጣሁ ነኝ? ብሎ መጠየቅ ከሁላችንም የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው፡፡
በትብብር እና በጋራ መንፈስ ችግራችንን እየፈታን፣ አገልገሎት አስጣጣችንን እያዘመን ወደ ፊት ከተራመድን የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረጋችን አይቀሬ ነው፡፡
እንኳን ለአገልግሎት ቀን በሰላም አደረሳችሁ
ጳጉሜን 01/2015 ዓ.ም
More Stories
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ