የ”ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ መድረክ መካሔድ ጀመረ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 30/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዘቦች ክልል ትምህርት ቢሮ የ”ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ መደረክ አካሂዷል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዘቦች ክልል ትምህርት ቢሮ የ2015 የትምህርት ልማት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ እና 2016 የ”ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ መድረክ በታርጫ አካሂዷል።
በንቅናቄው መድረክ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል የሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ 350 ሺህ በላይ የህበረተሰብ ተሳትፎ የትምህርት መሠረተ ልማት ለማሟላት፣ የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻለ ከፍተኛ ስራ መሰራቱን አመላክተዋል።
እስከ አሁን ድረስ በተካሄደው ንቅናቄ የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን ጠቁመው፥ በታየው ውጤት መዘናጋት ሳይፈጠር በዚህ መቀጠል አለበት ብሎዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማርቆስ ቡልቻ በበኩላቸው፥ መንግስት በትምህርት ዘርፍ የሚታየውን የትምህርት ጥራት ጉድለትን ለማሻሻል የጀመረውን ራዕይ እውን ለማድረግ በክልሉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ይሰራል ብለዋል።
አቶ ማርቆስ የክልሉ 2015 አፈጻጸም ሪፓርት እና የ2016 ዕቅድ ለመደረኩ ያቀረቡ ሲሆን፥ በመድረኩ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ የዞን አስተዳዳረዎች፣ የትምህርት መምሪያ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድሞዋል።
አዘጋጅ: አንዱዓለም ኡማ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ