24 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ ነው
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 10/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) መንግስት የኑሮ ወድነትን ለማሻሻል እና ገበያን ለማረጋጋት ተከታታይነት ያለው እርምጃ አንደሚወስድ ቃል በገባው መሠረት 24 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ የተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እየተጓጓዘ እንደሚገኝ ተገለጸ።
የምግብ ዘይቱ በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አማካኝነት በሁለት ምዕራፍ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ሲሆን፣ ይህ የፍጆታ ዕቃ በዋነኝነት የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግስት ግዢ የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል።
በማጓጓዝ ስራው የጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እንዲሁም ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ጋር በመቀናጀት በተቀላጠፈ መልኩ እየተሰራ እንደሆነ እና በመጀመሪያ የኦፕሬሽን ምዕራፍ 11 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ መላክ መቻሉ ተገልጿል።
በሁለተኛው ምዕራፍ 13 ሚሊዮን የምግብ ዘይት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ አገር ቤት እንዲገባ ብርቱ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘ መረጃ ያመለክታል::

More Stories
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለተለያዩ አገልግሎት ያስገነባቸውን ዘመናዊ ኮምፕሌክሶችን አስመረቀ
በጎፋ ዞን ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የበጋ ማጠቃለያና የክረምት በጎ ስራ ማስጀመሪያ መረሃ-ግብር ተካሄደ
በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ሀብት መሰብሰብ መቻሉ ተገለጸ