የደሬቴድ ዲጂታል ሚዲያ የነሐሴ 10/2015 ዓ.ም የዕለቱ ዋና ዋና ዜናዎች፡-
👉መንግስት የኑሮ ወድነትን ለማሻሻል እና ገበያን ለማረጋጋት ተከታታይነት ያለው እርምጃ አንደሚወስድ ቃል በገባው መሠረት 24 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ እንደሚገኝ ተገለጸ።
👉የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡
👉በክልሉ 697 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ ተናገሩ።
👉ከ84 ሚሊየን ብር በላይ የመንግስትና የህዝብ ሀብት ከምዝበራ ማዳን መቻሉን የሀዲያ ዞን ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ጥምረት አስታወቀ።
👉ኢትዮጵያ ከፊሊፒንስ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሻ በፊሊፒንስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሰየሙት ደሴ ዳልኬ ገለጹ።
👉በቤንች ሸኮ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት በህብረተሰብ ተሳትፎ የ60 ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ታቅዶ ወደተግባር መገባቱን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።
👉በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከ99 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ