“የዘመነ ክህሎት ስነ ምህዳር ለዘላቂ ስራ እድል” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው
“የዘመነ ክህሎት ስነ ምህዳር ለዘላቂ ስራ እድል” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት፤ የስራ ፈጠራ አማራጮችን ወደ ውጤት መቀየር የሚያስችሉ አሰራሮችን በመተግበር ስራ አጥነትን ለመቅረፍ እየተሰራ ይገኛል።
በክልሉ የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በአካባቢው የሚገኙ ፀጋዎችን ለይቶ መጠቀም የሚያስችል ዕቅድ በማዘጋጀት ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድልን ለመፍጠር ትኩረት መደረጉንም ገልጸዋል።
በመድረኩ ከክልል፣ ከዞንና ከልዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ አስቻለው አማረ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዓመታት ለሚደረጉ የኢንዱስትሪ ሽግግሮች ግብርና መሠረት ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ተናገሩ
የህግ ባለሙያዎችን ብቃትና ክህሎት ማጎልበት ለውጤታማ የፍትህ አገልግሎት ወሳኝ ነው – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የመሬት አስተዳደር ሥርዓትን በማዘመን የልማት እና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት መሠራት እንዳለበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አሳሰቡ