የመሬት አስተዳደር ሥርዓትን በማዘመን የልማት እና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት መሠራት እንዳለበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አሳሰቡ
የክልሉ መሬት አስተዳደር ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ክንውንና የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገምግሟል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሬት አስተዳደር ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ተፈሪ አባተ፤ ውስን የሆነውን የመሬት ሐብት በአግባቡ በመመዝገብ እና ባለቤትነትን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው ብለዋል።
የመሬት ሐብትን ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ከይገባኛል ክርክር ነጻ በማድረግ የዘርፉን ገቢ ለማሳደግ የተጀመረው ተግባር ውጤት እያመጣ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ተፈሪ፤ በየደረጃው ያለው አመራር ለዕቅዱ መሣካት በትኩረት እንዲሠራ አሳስበዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በመድረኩ ተገኝተው እንዳሉት፤ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ በዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች መቀረፍ እንዳለባቸው ገልጸው ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓትን በመዘርጋት የከተማ ዕድገትን በተቀናጀ ሁኔታ ማፋጠን ይገባል።
የክልሉን የመልማት አቅም ታሳቢ በማድረግ ከሌብነት፣ ከብልሽት እና ድለላ አሰራር ነጻ በማድረግ አመራሩ በተጠያቂነት መንፈስ መሥራት እንዳለበትም ኢንጂነር ወንድሙ መክረዋል።
ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ክንውን፣ የ2019 በጀት ዓመት የሶስት ወራት አፈጻጸም ክንውን እንዲሁም የቀጣይ 100 ቀናት ዕቅድ ለባለድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ዘጋቢ: ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ሁሉንም ተግባራት የፖሊስን ክብር በሚያስጠብቅ መንገድ ማከናወን እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ተናግረዋል
ያሉንን የገቢ አማራጮች አሟጦ በመጠቀም የሕዝቡን እያደገ የመጣ የልማት ጥያቄዎች መመለስ እንደሚገባ የጋሞ ዞን አስተዳደር አሳሰበ
ሙስሊሙን ወጣት በወንድማማችነት መንፈስ በማሰባሰብ በእስላማዊ እውቀትም ሆነ በኢኮኖሚው መስክ ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል አስታወቀ