የህዝቦችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን ወሳኝ ነው – አቶ ኡስማን ሱሩር

የህዝቦችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን ወሳኝ ነው – አቶ ኡስማን ሱሩር

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም (ደሬቴድ) የህዝቦችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን ወሳኝ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ገለፁ።

በአቶ ኡስማን ሱሩር የተመራ ልኡክ በስልጤ ዞን በምራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በስርአት ምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም የተሰሩ ውጤታማ የግብርና ስራዎች ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

በጉብኝት ፕሮግራሙም የተለያዩ የክልል የዞንና የወረዳ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ዘጋቢ: ረዚቃ ተመስገን – ከሆሳዕና ጣቢያችን