የአርሰናል እና ሊቨርፑል ተጠባቂ ጨዋታ!
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር ላይ ተጠባቂ የሆነው እና መላው የእግር ኳስ ዓለም ትኩረት የሰጠበት ተጠባቂ ጨዋታ ዛሬ ማምሻውን በሊቨርፑል እና አርሰናል መካከል በአንፊልድሮድ ይካሄዳል።
በዚህ ሳምንት መርሃ ግብር መሪው ማንቸስተር ሲቲ በትናንትናው ዕለት በብራይተን መሸነፉን ተከትሎ፤ የደረጃ ሰንጠረዡን መሪነት በድጋሚ የመረከብ ወርቃማ ዕድል እጁ ላይ የወደቀው አርሰናል ከአንፊልድ ስታዲየም ምን ይዞ እንደሚወጣ በጉጉት ይጠበቃል።
15 ነጥቦችን ይዞስ 5ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሊቨርፑል በሜዳው አርሰናል ላይ ያለውን የበላይነት ማስቀጠል ይችላል ወይ የሚለውም ጉዳ ሌላኛው የጨዋታው አጓጊ ርዕሰ ጉዳይ ነው።
አርሰናል የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ከሊቨርፑል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 9 በማስፋት መሪነቱን ከማንቸስተር ሲቲ ይረከባል።
ሊቨርፑል የሚያሸንፍ ከሆነ ደግሞ ከአርሰናል እና ከሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 3 ዝቅ የሚያደርግ ሲሆን፣ በዋንጫ ፉክክሩ ላይ በድጋሚ ነፍስ የሚዘራ ይሆናል።
ጨዋታው ምሽት 1፡30 ላይ መካሄድ ይጀምራል።
ባለሜዳው ሊቨርፑል ወደዚህ ጨዋታ የሚገባው በጥሩ መነቃቃት ላይ ሆኖ ነው። በሳምንቱ አጋማሽ በካራባዎ ዋንጫ ቼልሲን በመለያ ምት ከውድድሩ ውጪ ማድረግ የቻለው ሊቨርፑል፣ በፕሪሚየር ሊጉም በደረጃ ሰንጠረዡ ከእሱ በላይ የነበሩትን ብሬንትፎርድን እና ብራይተንን በተከታታይ በማሸነፍ ግስጋሴውን ቀጥሏል።
በተለይም አጥቂው አሌክሳንደር ኢሳክ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን በማስቆጠር አስፈሪ ወቅታዊ አቋም ላይ ይገኛል። ሊቨርፑል ዛሬም ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠውን አርሰናል ማሸነፍ ከቻለ፤ እ.አ.አ ከ2009 ወዲህ ከማንቸስተር ዩናይትድ በመቀጠል በሊጉ ታሪክ ሦስት ምርጥ አራት ውስጥ የተቀመጡ ቡድኖችን በተከታታይ ያሸነፈ ሁለተኛው ክለብ በመሆን አዲስ ታሪክ ይጽፋል።
ሆኖም በሊቨርፑል በኩል እንደ ሁጎ ኤኪቲኬ፣ ኮኖር ብራድሌይ፣ ጄሬሚ ፍሪምፖንግ እና ወጣቱ ጆቫኒ ሌኦኒ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ መሆናቸው ፈተና ፈጥሮበታል።
የሻምፒዮንነቱን ክብር ለማስጠበቅ ከባድ ፉክክር ውስጥ የሚገኘው የሚኬል አርቴታው አርሰናል፤ በሳምንቱ አጋማሽ በካራባዎ ዋንጫ ባልተጠበቀ ሁኔታ በፍሊትዉድ ታውን ተሸንፎ ከውድድሩ መሰናበቱ የቡድኑን መመንፈስ ሊፈትነው ይችላል።
ከዚህም በላይ መድፈኞቹ እ.ኤ.አ ከ2012/13 የውድድር ዘመን ወዲህ ባደረጓቸው ያለፉት 14 ዓመታት የፕሪሚየር ሊግ የአንፊልድ ጉዞዎች አንድም ድል አላስመዘገቡም።
በአንፊልድ ካደረጓቸው 13 ጨዋታዎች 5 ጊዜ አቻ ሲወጡ፣ 8 ጊዜ ደግሞ ተሸንፈዋል።
ለዚህ ዛሬ ለሚደረገው ወሳኝ ጨዋታ አርሰናል ቁልፍ ተጫዋቾቹን አያሰልፍም። ቡካዮ ሳካ በጉዳት ሲገለል፣ ታዳጊው ማክስ ዳውማን ደግሞ በቅጣት ከሜዳ ይርቃሉ።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ዓለምን ያስደመሙት የ90 ዓመቱ ጃፓናዊ የአካል ብቃት ተወዳዳሪ
ቼልሲ ማንቸስተር ዩናይትድን በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመለሰ
ሃሪ ኬን ኪሊያን ምባፔን በ28 ነጥብ ብቻ በመበለጥ ባሎንዶሩን ማሸነፉ ይፋ ሆነ