የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበር በህዝቦች መካከል አንድነትና  የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር የሚያግዝ መሆኑ ተገለፀ

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበር በህዝቦች መካከል አንድነትና  የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር የሚያግዝ መሆኑ ተገለፀ

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበር በህዝቦች መካከል አንድነትና  የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር የሚያግዝ መሆኑን የዋካ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል “በብዝሃነት የደመቀች፤ በምክክር የጸናች ስልጡን ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

በዳውሮ ዞን  የዋካ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የብሔር፣ ብሔርቦች በዓል አከባበር መሪ ዕቅድ ዙሪያ  ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የዋካ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ እስክንድር ተፈራ እንደገለፁት፤ የበዓሉ መከበር ብዝሃነትን በማስተናገድ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህገ መንግስታዊ ዋስትና የሚያረጋግጥና በህዝቦች መካከል አንድነት የሚፈጥር ነው ብለዋል።

በዓሉ ሲከበር ህገ-መንግስትን በሚገባ ከማወቅና ለህገ-መንግስታዊነት ከመገዛት አኳያ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን መቅረፍ የሚያስችሉ የፓናል ውይይቶች እና የተለያዩ የስልጠና መድረኮች እስከታችኛው መዋቅር እንዲዘጋጁ በማድረግ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እንደሚሰራ አፈ-ጉባኤው ገልጸዋል።

‎በከተማ አሰተዳደሩ ሁሉም ቀበሌዎች በዓሉ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር የተመረጡ አብይ ኮሚቴዎችና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀው፤ የበዓሉ ዓላማ ሳይዛባ እንዲከበር ኮሚቴው ጉልህ ሚና እንዳለው በመረዳት በዓሉ በድምቀት እንዲከበር  ም/ቤቱ ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡

የከተማው የመንግስት ረዳት ተጠሪና  የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ መምህር ባንተይዋሉ  ፎላ እንዳሉት፤ በህዝቦች መካከል መከባበርን፣ መቻቻልን እና ሊጠቅሙ የሚችሉ ዕሴቶችን አንዱ ከአንዱ በመቅሰም የሁላችን ቤት የሆነችውን ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ በዓሉ እንደሚጠቅም በመረዳት ልናከብር ይገባል ብለዋል።

የህዝባችንን ፍላጎትና መሠረታዊ የሆኑ ባህሎችን አውጥተን የምናሳየውና ከሌላው ልምድ የምንወስድበት ቀን ስናከብር ዕሴቶቻችንና ባህሎችን ለሀገርና ለዓለም ማስተዋወቅ ከሁላችን ይጠበቃል ብለዋል መምህር ባንተይዋሉ።

የከተማ አስተዳደሩ ፍትህና ፀጥታ ጽ/ቤት የህግ ባለሙያ አቶ ህዝቅኤል  በተላ የህገ መንግስት አስተምሮ በተመለከተ ባቀረቡት ጽሑፍ እንደገለጹት፤ የሕገ-መንግስት አስተምህሮ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ተደራሽ ተደርጎ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመው፤ ዘንድሮም እንደወትሮው በቁርጠኝነትና በተነሳሽነት ወደ ሥራ በመግባት በታቀደው ዕቅድ መሰረት የህገ መንግስትና  የፌዴራልዝም አስተምህሮ ስራ ትኩረት በመስጠት ይሰራል ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ፤ ከዛሬ ጀምሮ የቅስቀሳ ስራዎችን የሚዲያ  አማራጮችን  በመጠቀም አጠናክሮ በመስራት  በዓሉ በስኬት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል።

በመርሐ-ግብሩ ከከተማ  አስተዳደሩ የተውጣጡ የፍትህና የምክር ቤት ተቋማት ባለሞያዎች እና ባለድርሻ አካላት  የተገኙ ሲሆን፤ በዓሉ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ በሰላም ተከብሮ እንዲውል የሚያስችል ሁነት ላይ ከኮሚቴዎች ጋር ተወያይተው አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል።

አዘጋጅ፡  አንዱዓለም ኡማ – ከዋካ ጣቢያችን