ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን በተገኙበት በሸካ ዞን ከተለያዩ ማሕበረሰብ ተወካዮች ጋር የትውውቅና ውይይት መድረክ በቴፒ ከተማ መካሄድ ጀምሯል
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን በተገኙበት ከሸካ ዞን ከተለያዩ ማሕበረሰብ ተወካዮች ጋር በቴፒ ከተማ የትውውቅ እና ውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩ በቅርብ በአዲስ መልክ የተመሰረተውን የክልሉ መንግስት ከዞኑ ህዝብ ጋር ከማስተዋወቅ ባሻገር በልማት፣ በሰላምና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ተነጋግሮ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።
ውይይቱ በሕዝቡና በክልል መንግስት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር ከማድረግ ባለፈ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ያስችላል።
በዚህ መድረክ ላይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን፣ የክልሉ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ: ታሪኩ ታደሰ – ከማሻ ጣቢያችን
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን በተገኙበት በሸካ ዞን ከተለያዩ ማሕበረሰብ ተወካዮች ጋር የትውውቅና ውይይት መድረክ በቴፒ ከተማ መካሄድ ጀምሯል

More Stories
የአንድ ማህበረሰብ ቋንቋ ለትውልድ እንዲተላለፍ እና በጽሑፍ እንዲበለጽግ የቋንቋ ሰዋሰው ጥናት ወሳኝ ሚና አለው – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ባህልና ስፖርት ቢሮ
ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ጂንካ ከተማ ገቡ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የብሄረሰቦች ምክር ቤት 21ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው