የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከፍተኛ ልዑክ ለሥራ ጉብኝት ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ገባ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር በአቶ ፍቅሬ አማን የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ልዑክ ለሥራ ጉብኝትና ለሕዝባዊ ውይይት ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ገብቷል።
ልዑኩ ቴፒ ከተማ ሲደርስ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ወልዴን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞኑና የከተማው አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በተጨማሪም ልዑኩ በነገው ዕለት ከተለያዩ የማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር የትውውቅና የጋራ ውይይት እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ: በዛብህ ታደሰ – ከማሻ ጣቢያችን

More Stories
መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት እውን ማድረግ እንዲቻል ተመራቂ ተማሪዎች በተመረቁበት የሙያ መስክ ማህበረሰቡን በታማኝነት ሊያገለግሉ ይገባል ሲሉ አቶ አንነህ ፈቃዱ ገለጹ
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማንና ካቢኔያቸው ለሕዝባዊ ውይይት ሚዛን አማን ከተማ ገቡ
በካፋ ዞን “ማንሰራራት ለዞናችን ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የመደመር መንግስት የትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው