ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

ዋና ፀሐፊው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡

ቀጣዩ የሥራ ዘመናቸው የስኬት እንዲሆንላቸውም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢጋድ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጋር ለሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለቀጣናዊ የጋራ ብልጽግና በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡