የጌዴኦ ልማት ማህር በዲላ ከተማ የአጼ ዳዊት ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታ እያከናወነ ይገኛል
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ የጌዴኦ ልማት ማህበር በጥንታዊው አጼ ዳዊት ትምህርት ቤት ቅር ግቢ ውስጥ የማስፋፊያ ግንባታ እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
የልማት ማህበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብዙነህ ንጉሴ አጼ ዳዊት ትምህርት ቤት በ1945 ዓ.ም እንደተመሠረተና ጥንታዊ መሆኑን በመጥቀስ ካስቆጠረው ዕድሜ አንጻር ብዙ ዕድሳት፣ ልማትና ማስፋፊያ ሳይደረግለት መቆየቱን አስረድተዋል።
የአጼ ዳዊት 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮጀክት ግንባታ ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም የተጀመረ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት። 4 ክፍሎች ያሉትና እያንዳንዱ ክፍል 200 ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑንም አክለዋል።
ግንባታው በ9 ቀናት ውስጥ ከ39 መቶ በላይ መድረሱን ተገልጿል።
ለ2016 ዓ.ም ተማሪዎችን ተቀበሎ የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችል ቁመና ላይ ይገኛልም ተብሏል፡፡
የልማት ማህበሩ ሰብሳቢ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ የከተማው ሕብረተሰብ፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶች እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ ለትምህርት ጥራት የሚደረገው ጥረት እንዲረጋገጥ የኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡ እስራኤል ብርሃኑ – ከፍስሐገነት ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ