ከ29 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገናኙት ኢትዮጵያ እና ሴኔጋል

ከ29 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገናኙት ኢትዮጵያ እና ሴኔጋል

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳው ባህር ዳር ስታዲየም ሴኔጋልን ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ይገጥማል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ በሱዳን 1ለ0 መሸነፉ ይታወሳል።

የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ደግሞ በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ከሞዛምቢክ ጋር 1ለ1 ነው የተለያየው።

ዋልያዎቹ በወቅቱ የፊፋ ሀገራት ደረጃ ከዓለም 143ኛ ከአፍሪካ 44ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሲሆን የቴራንጋ አንበሳዎቹ ደግሞ ከዓለም 19ኛ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሩ ምድር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታን ያከናውናል።

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት”በሜዳችን እና በህዝባችን ፊት የምንጫወት መሆናችን ለእኛ በጥሩ መልኩ የሚነሳ ነው” ብለዋል።

የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆኑት ፓትሪክ ቬይራ በበኩላቸው”ጨዋታው 0ለ0 ነው የሚጀምረው፣ተጋጣሚያችንን አክብረን እንጫወታለን” ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኩል አጥቂው መስፍን ታፈሰ በሁለት ቢጫ እንዲሁም አማካዩ በረከት ወልዴ በጉዳት ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ሆነዋል።

በሴኔጋል ብሔራቡድን በኩል እንዲሁ የክሪስታል ፓላሱ ኢስማኤላ ሳር እና የማቸስተር ሲቲው ኢልማን ኒዲዬ ባለፈው ጥር በአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ባሳዩት ያልተገባ ባህሪ ምክንያት ሁለት ጨዋታ በመቀጣታቸው ዛሬ አይሰለፉም።

ሁለቱ ሀገራት ከ29 አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ይገናኛሉ።

ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በፈረንጆቹ 1997 በተመሳሳይ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሲሆን በወቅቱ ሴኔጋል 3-0 አሸንፋ ነበር።

የዛሬውን ጨዋታ ካሜሮናዊው ዊሊ ስቲፈን ኒጋህ በመሃል ዳኛነት የሚመሩት ይሆናል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ