አትሌት ልቅና አምባው ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አስገኘች!

አትሌት ልቅና አምባው ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አስገኘች!

በዴንማርክ ኮፐንሀገን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር አትሌት ልቅና አምባው ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች።

በሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ውድድር በመሳተፍ ነው አትሌት ልቅና አምባው ለሀገሯ የወርቅ ሜዳልያ ያሳካችው።

አትሌቷ 14 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ውድድሩን በማጠናቀቅ የዓመቱን ምርጥ ሰዓቷን ማስመዝገብ ችላለች።

ረፋድ ላይ በተደረገ የአንድ ማይል ውድድር አትሌት ፍሬወይኑ ሀይሉ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጲያጰየብር ሜዳልያ ማሳካት ችላለች።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ