ለህዝቡ ትክክለኛ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እያከናወነ ያለውን ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ገለጸ

ለህዝቡ ትክክለኛ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እያከናወነ ያለውን ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ገለጸ

‎የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት አቅድ ላይ ትኩረት ያደረገ መድረክ አካሂዷል።

‎በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልደ (ዶ/ር)፤ መንግሥት ትክክለኛ መረጃ ለህዝቡ ተደራሽ ከሚያደርግባቸው ሴክተሮች መካከል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አንዱ እንደመሆኑ በ2018 በጀት ዓመት ተአማኒነት ያለው መረጃ ለህዝቡ ተደራሽ ከማድረግ ረገድ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

‎አክለውም ወቅታዊ ሀገራዊ፣ ክልላዊ እና ዞናዊ ሁነቶችን በመከታተል ህዝቡ መረጃ እንዲያገኝ የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሰራው ሥራ ውጤታማ እንደነበር ገልጸው እነዚህ ተግባራት በቀጣይም ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አንስተዋል።

‎የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ወ/ሮ ዜና ማሞ በበኩላቸው÷ ተቋሙ በተሰጡት ዋና ዋና ግቦች መነሻ ትክክለኛ መረጃ በማሰራጨት እና መንግሥት በሚያወጣቸው ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች ላይ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል።

‎በተለይ ህዝቡ በልማት ሥራዎች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥረት ከማድረግ ባሻገር በዞኑ የሚገኙ እምቅ ሀብቶችን የማስተዋወቅ ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል።

‎በ2018 የምርጫ ሥራ እና የጌዴኦ ብሄር ዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል አከባበርን በተመለከተ የነበሩ ሁነቶችን ከማሰራጨት ረገድ በርካታ ተግባራት መከናወኑንና በዚህም ውጤታማ ሥራ መሰራቱን አስረድተዋል።

‎አክለውም በ2018 የነበሩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

‎በመድረኩ በ2018 በጀት ዓመት የነበሩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን በጥልቀት በመገምገምና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

‎የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በ2018 በጀት ዓመት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ክፍተቶችን ለማረም የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

‎ዘጋቢ: እንግዳየሁ ቆሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን