ቶትንሃም በአስቶንቫላ ተሸነፈ
በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ቶትንሃም ሆትስፐርስ በሜዳው በአስቶንቫላ 3ለ2 ተሸንፏል።
ለእንግዳው ቡድን አስቶንቪላ የማሸነፊያ ጎሎችን ጇኦን ማንዛምቢ፣ ኒኮላስ ጃክሰን እና ኤሚሊያኖ ቡንዲያ ከመረብ አሳርፈዋል።
ለባለሜዳው ቶትንሃም ምንም እንኳን ከሽንፈት መታደግ ያልቻሉ ቢሆንም በሊጉ የዚህ ዓመት የመጀመሪያ የሆኑለትን ጎሎች ኮነር ጋላገር እና ቫን ሃከን አስቆጥረዋል።
አስቶንቪላ በአዲሱ የውድድር ዓመት የመጀመሪያ የፕሪሚዬር ሊግ ድሉን ነው ማሳካት የቻለው።
ቶትንሃም በአንፃሩ እስካሁን ያከናወናቸውን አምስቱን የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
አትሌት ልቅና አምባው ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አስገኘች!
አባቱን በደስታ ያዘለለው ልጅ
ሆዜ ሞሪንሆ እና ዲዬጎ ሲምዮኔ ከ12 ዓመታት በኋላ በማድሪድ ደርቢ ይፋለማሉ