ቢሮው በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ልኬት ስራ በማጠናቀቅ የይዞታ ማረጋገጫ ለአርሶአደሮች አስረከበ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሬት አስተዳደር ቢሮ በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ በጂኦ ስፓሻል ዘርፍ በCAM-LA ፕሮጀክት የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ልኬት ስራ አጠናቆ የይዞታ ማረጋገጫ ለአርሶአደሮች አስረክቧል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ በመርሃ ግብሩ እንደተናገሩት፣ ቢሮው የአርሶአደሩን የመሬት ይዞታ ባለቤትነትን በማረጋገጥ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ ነው።
እንደ አቶ ሰብስቤ ገለጻ፤ የመሬት ይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫው ባለንብረትነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ አርሶአደሮች ተበድረው ሀብት ማፍራት የሚችሉበት ነው።
የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪና ተወካይ አቶ ዳንኤል ሽፈራው በበኩላቸው፤ የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚከናወኑ ተግባራት ውጤት እየተመዘገቡ ናቸው ብለዋል።
አሁን ላይ በመሬት ልኬት ዘርፍ እየተሰራ ያለው ተግባር አበረታች መሆኑንም አቶ ዳንኤል አመላክተዋል።
የገደብ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ታደሰ፤ ልኬቱ ለአርሶአደሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የጎላ ፋይዳ እንዳለው ነው የተናገሩት።
ልኬቱ ተጠናቆላቸው የማረጋገጫ ደብተር የወሰዱ አርሶአደሮች በበኩላቸው፤ ከመሬት ባለቤትነት ጋር ተያይዘው ይመጡ የነበሩ ችግሮችን የፈታና ተበድረው ራሳቸውን እንዲቀይሩ በር የከፈተ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ: እስራኤል ቅጣው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
ቢሮው በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ልኬት ስራ በማጠናቀቅ የይዞታ ማረጋገጫ ለአርሶአደሮች አስረከበ

More Stories
ብዝኃ ህይወትን ቀጣይነት ባለው መንገድ በማልማትና በመንከባከብ ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል – አቶ ተፈሪ አባተ
የዘይሴ ብሔር ዘመን መለወጫ “ቡዶ ኬሶ” በዓል በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ኤልጎ ቀበሌ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት መሬት አስተዳደር ቢሮ በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ሐሎሀርጡሜ ቀበሌ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደካማ እናት ያስገነባውን ቤት ከነሙሉ የቤት ቁሳቁስ አስረከበ