የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት መሬት አስተዳደር ቢሮ በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ሐሎሀርጡሜ ቀበሌ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደካማ እናት ያስገነባውን ቤት ከነሙሉ የቤት ቁሳቁስ አስረከበ
ወ/ሮ እታገኘሁ ጌታሁን በገደብ ወረዳ የሐሎሀርጡሜ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። ባለቤታቸውን በሞት ከተነጠቁ ዓመታትን አስቆጥረዋል። ልጆቻቸውን ለማሳደግ ብቻቸውን በርካታ ዓመታትን ሲታትሩ የቆዩ ሲሆን በወደቀና በሚያፈስ ቤት ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ይኖሩ እንደነበር ነው የሚናገሩት።
አሁን ላይ የበርካቶችን እንባ እያበሰ በሚገኘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት መሬት አስተዳደር ቢሮ ቤታቸውን ገንብቶ ከነሙሉ የቤት እቃ በማስረከቡ ከጭንቀታቸው ማረፋቸውን ገልጸዋል።
በዚህም መደሰታቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ እታገኘሁ የክልሉን መንግሥት የመሬት አሰተዳደር ቢሮና ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት መሬት አስተዳደር ቢሮ የኢንቨስትመንትና መሬት ልየታና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ተወካይ እና የበጎ አገልግሎቱ አስተባባሪ አቶ ታምራት ጌታቸው እንደተናገሩት፤ የቤቱ ግንባታና የቤት ቁሳቁሱ ከ1.4 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የወጣበትና አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን በወረዳው በተደራጁ ማህብራት የግንባታው ግብአት ስራው መፈጸሙ በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍም አስተዋጽኦ አበርክቷል።
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበራዊን ዘርፍ ከመደገፍ አንጻር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነውም ብለዋል።
የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዋና አማካሪና የዋና አስተዳዳሪው ተወካይ አቶ ዳንኤል ሽፈራው በበኩላቸው፤ ቢሮው ለሌሎች አርአያ በሚሆን መልኩ ለአቅመ ደካማዋ ቤት ገንብቶ በማስረከቡ በዞኑ አስተዳደር ስም አመስግነዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ በክረምት ወራት የተሰሩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር መሆኑን ያሳየበት ነው ብለው፤ ቢሮው ለወ/ሮ እታገኘሁ በ24 ቀናት ውስጥ ቤት ገንብቶ ማስረከቡን ገልጸዋል።
ዘጋቢ: እስራኤል ቅጣው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት መሬት አስተዳደር ቢሮ በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ሐሎሀርጡሜ ቀበሌ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደካማ እናት ያስገነባውን ቤት ከነሙሉ የቤት ቁሳቁስ አስረከበ

More Stories
የዘይሴ ብሔር ዘመን መለወጫ “ቡዶ ኬሶ” በዓል በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ኤልጎ ቀበሌ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል
የወላይታ ብሄር የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም መካሄድ ጀምሯል
የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ፍትሀዊ በሆነ መልኩ ተደራሽ ለማድረግና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ወሳኝ ነው – አቶ መዝረዲን ሁሴን