የሪያል ማድሪድ ትኩረት በ ማንችስተር ዩናይትድ ታዳጊ ጄጄ ጋብርኤል ላይ

የሪያል ማድሪድ ትኩረት በ ማንችስተር ዩናይትድ ታዳጊ ጄጄ ጋብርኤል ላይ

ማንችስተር ዩናይትድ ወጣቱን የዕድገት ማዕከል (አካዳሚ) ተጫዋች ጄጄ ጋብሬልን የማቆየት ከፍተኛ ፈተና ላይ ወድቋል።

እድሜው 15 ዓመት ብቻ የሆነው ይህ ተሰጥኦ ያለው አጥቂ ከዩናይትድ ጋር ያለውን ምዝገባ በአስቸኳይ መሰረዝ እንደሚፈልግ በይፋ አሳውቋል።

ሪያል ማድሪድ ከባርሴሎና፣ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና ባየር ሙኒክ ጋር በመወዳደር የፊት መስመር ተጫዋቹን ለማዘዋወር ጠንካራ ርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።

የስፔኑ ክለብ ተጫዋቹን ወዲያውኑ በመውሰድ በቀጥታ ከዋናው ቡድን ጋር ቅርብ ወደሆነው እና በስፔን ሦስተኛ የሊግ ዕርከን በሚወዳደረው የሪያል ማድሪድ ካስቲያ ቡድን ጋር አካል ለማድረግ አቅዷል።

ጋብሬል በቀጣይ ጥቅምት 6 ቀን 16 ዓመቱ የሚሞላው ሲሆን፣ በዩናይት ከዋናው ያለው የዕድገት ምዕራፍ ቃል በተገባለት ልክ እንዳልተጠበቀ በማመን በዩናይትድ ላይ ቅር መሰኘቱ ተሰምቷል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹ ትናንት ምሽት ከብራይተን ጋር በተደረገው የካራባኦ ካፕ ጨዋታ ተሰልፎ በክለቡ ታሪክ ለዋናው ቡድን ተሰልፎ መጫወት የቻለ በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች እንዲሆን እቅድ ተይዞለት እንደነበር ቢገለፅም ፣ የተጫዋቹ አለመስማማት እና አሁን ላይ ከክለቡ ጋር ልምምድ ባለመስራቱ በቡኑ ውስጥ ሳይካተት በመቅረቱ ሁኔታው ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል።

ዩናይትድ ተጫዋቹን አሁንም የማቆየት ተስፋውን ሙሉ በሙሉ አልቆረጠም፤ ነገር ግን ተጫዋቹ ልቀቁኝ ብሎ ጥያቄ ማቅረቡ ቀጣዩ ሂደት ከፍተኛ ትኩረት ስቧል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ