በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡታጅራ ክላስተር የጳጉሜ 3 “የጽናት ቀንን” በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ፣ የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር፣ የመስቃን ወረዳ ፖሊስ አባላት፣ የቡታጅራ አካባቢ ማረሚያ ተቋም የፖሊስ አባላትና የመስቃን ወረዳ ሚሊሻ የጽናት ቀንን በማስመልከት በከተማው የሰልፍ ትርዒት አሳይተዋል።
ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኘው በዚህ መርሀ ግብር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ባዩሽ ተስፋዬ ሌሎች የክላስተሩ አመራሮች ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞንና የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የመስቃን ወረዳ አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ ለበርካታ እልፍ ዘመናት በጽናት ፣ በጥንካሬ እና በብርታት እየተሻገረች የመጣች ጠንካራ ሀገር መሆኗን የሚገልጹ መልዕክቶች የተላለፉበት መድረክ እየተካሄደ ነው ።
ጳጉሜ ሶስትን ምክንያት በማድረግ “የጽናት ቀን” ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ እንዳልካቸው ጌታቸው ኢትዮጵያ ከተረጂነት ለመውጣት በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከማድረግ ጨምሮ በለውጡ መንግስት የጸናች ሀገር ለመገንባት እየሰራች ነው ብለዋል።
የጽናት ቀን የሆነውን ጳጉሜ 3ን ስናከብር የቀጣይ ጉዞአችን ስኬታማ ለማድረግ ቃል የምንገባበት ነው ብለዋል።
2018 ዓ.ም ትልልቅ ድሎች የተመዘገቡበት ከቁልቁለት ጉዞ ወጥተን ወደ እድገት መስፈንጠር የተጀመረበት ዓመት እንደነበርም ጠቅሰዋል።
በመርሀ ግብሩ የተገኙ ሁሉ ኢትዮጵያ ወደ እድገትና ብልጽግና ለማሸጋገር የሚገጥሙ ፈተናዎችን በጽናት ለመጋፈጥ ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል።
ዘጋቢ፡ አብደላ በድሩ

More Stories
“የፅናት ቀን” በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እየተከበረ ነው
ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የጉራጌ ዞን አስተዳደር ህንፃ እየተመረቀ ነው
በማህበራት ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ ወጣቶች ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ