የብደርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበራት የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮችን ላይ የሚያደርጉት አበረታች ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለጸ

የብደርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበራት የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮችን ላይ የሚያደርጉት አበረታች ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ጳጉሜን 02/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የብደርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበራት የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮችን ላይ የሚያደርጉት አበረታች ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የፌደራል ህብረት ስራ ልማት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

‎የሁሉ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር 17ኛውን ቅርንጫፍ በአርባምንጭ ከተማ በይፋ ስራ አስጀምሯል።

‎የሁሉ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መሳፍንት ደበበ፤ ማህበሩ በሀገር ደረጃ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ማህበረሰብን ጨምሮ 10 ቢሊዬን ብር በላይ ብድር በማመቻቸት 60 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።

‎አሁንም አካታች በሆነ መልኩ ብድርና ቁጠባ በማመቻቸት ህብረተሰቡ ከዘርፉ በይበልጥ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን ማሳደግ እንዲችል 17ኛውን ቅርጫፍ በአርባምንጭ ከተማ መከፈቱን ተናግረዋል።

‎የፌደራል ህብረት ስራ ልማት ኮሚሽን ተወካይ አቶ ኢብራሂም እስማኤል፤ በሀገሪቱ 18ሺህ በላይ ብድርና ቁጠባ ማህበራት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ከሚያደርጉ ሁሉ ብድርና ቁጠባ ማህበር ቀዳሚ መሆኑን ገልፀዋል።

‎የአርባምንጭ ከተማ የህበረት ስራ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባንቲርጉ ኮዮ በበኩላቸው ማህበሩ የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮናሚያ ችግርችን ለመቅረፍ በከተማው ቅርጫፍ መከፍቱ እንዳስደሰታቸው ገልፀው ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል።

‎የዕለቱ ተጋባዠ እንግዳና የአካባቢው የሀገር ሽማግሌ አቶ ሳዲቃ ሲሜ ማህበሩ በአካባቢው መከፈት የከተማውን ዕድገት ከማፋጠን በዘለለ ለወጣቶች የስራ ዕድል እንድፈጠር የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው እምነታቸውን ገልጸዋል ።

‎ዘጋቢ፡ እንጃ ገልሲሞ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን