የሊቨርፑል እና ኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቀቀ

የሊቨርፑል እና ኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቀቀ

በ2ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በአንፊልድ ሮድ ሊቨርፑል ከኖቲንግሃም ያደረጉት ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

በጨዋታው ኖቲንግሃምን ሁለቴ መሪ እንዲሆን ያስቻሉ ጎሎችን ዳን ንዶዬ እና ጊብስ ዋይት(በፍፁም ቅጣት ምት) አስቆጥረዋል።

ሊቨርፑልን ሁለት ጊዜ አቻ ማድረግ የቻሉ ግቦችን ደግሞ አሌክሳንደር ኢዛክ እና ቪክቶር ሙኖዝ አስገኝተዋል።

ስፔናዊው የመስመር አጥቂ ሙኖዝ የመጀመሪያ የሊግ ጎሉን አስቆጥሯል።

ሊቨርፑል በአዲሱ የውድድር ዓመት በፕሪሚዬር ሊጉ ሁለተኛ ተከታታይ የአቻ ውጤት አስመዝግቧል።

የዛሬው የአቻ ውጤት በፕሪሚዬርሊጉ የሊቨርፑልን ያለማሸነፍ ጉዞ አራዝሞታል።

የመርሲሳይዱ ክለብ አሁን በስድስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ምንም ማሸነፍ አልቻለም።

4 ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት ሲያጠናቅቅ፣ በ2 ጨዋታዎች ሽንፈትን አስተናግዷል።

ከዚህ የበለጠ ረጅም ጊዜ ድል አልባ ጉዞ ያደረገው እ.ኤ.አ በ2012 በመጋቢት እና መስከረም ወር መካከል የነበረው ነው።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ