አሊያንስ አርባ ምንጭ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1462 ተማሪዎችን አስመረቀ

አሊያንስ አርባ ምንጭ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1462 ተማሪዎችን አስመረቀ

በትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ የተሠማሩ ተቋማት መንግሥት የጀመረውን የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ መርሐ ግብር ተግባራዊነት በትኩረት እንዲሰሩ ተጠይቋል።

የአሊንስ ኮሌጅ ቦርድ ሰብሳቢ ረዳት ፕ/ር ሱልጣን ሁሴን፤ ኮሌጁ በብቃትና በክህሎት የበቁ ዜጎችን ከማፍራት አኳያ የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።

የኮሌጁ ዲን አቶ ፋሲል ሰሎሞን በበኩላቸው፤ ኮሌጁ ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን በምርምር እና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶቾ ባከናወነው ተግባር ከ50 ወገኖች በላይ ቀጠተኛ ተጠቃሚ ማድረጉን ገልጸዋል።

የትምህርት ዘርፍ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ህጻናት ከታች ጀምሮ ተኮትኩተው እንዲያድጉ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ኮሌጁ ትምህርትን በጥራት እየሰጠ መሆኑንም ሱልጣን ተናግረዋል።

ኮሌጁ ከሌሎች አጋር አካላት በተገኘ የ21 ሚሊዮን ብር ገንዘብ ድጋፍ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ ጎዳና ተዳዳሪዎችንና ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በማሰልጠን የሙያ ባለቤት ማድረጉንም አስረድተዋል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ እና የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ካንቲባ ተወካይ አቶ ማዶ መንገሻ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ የሀገሪቱን ብልጽግና ለማረጋገጥ ጥራት ያለው የትምህርት መስጠት ወሳኝ ነው።

በትምህርት ስልጠና ዘርፍ የተሰማሩ አካላት መንግሥት የጀመረውን የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ፓኬጆችን ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል አቶ ማዶ።

በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተዘጋጀላቸውን የዋንጫ እና ማበረታቻ ሽልማት ከክብር እንግዳው እጅ ተረክበዋል።

ዘጋቢ: ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን