በደቡብ ሬዲዮ እና ቴለቪዥን ድርጅት ዋካ ቅርንጫፍ FM 93.4 የተመሠረተበትን 14ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሰራተኞቹ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

በደቡብ ሬዲዮ እና ቴለቪዥን ድርጅት ዋካ ቅርንጫፍ FM 93.4 የተመሠረተበትን 14ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሰራተኞቹ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 21/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ሬዲዮ እና ቴለቪዥን ድርጅት ዋካ ቅርንጫፍ ሰራተኞች ዋካ FM 93.4 የተመሠረተበትን 14ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

በተቋሙ ቅጥር ግቢ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች የተተከሉ  ሲሆን ለአካባቢ ጥበቃ የሚኖራቸው ፋይዳም ጉልህ መሆኑ ተገልጿል።

የሚድያ ተቋማት  የተሰጣቸውን ተግባራት ብቻ ሳይሆን እንዲህ ባሉ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ለሀገራዊ ጥሪ የበኩላቸውን መወጣት እንደሚገባቸው ተመላክቷል።

ዘጋቢ፡ አዲስዓለም ታዬ – ከዋካ ቅርንጫፍ