በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የመረጃ፣ የቢዝነስና የመሰረተ ልማት ትብብር የሚያጠናክር ስምምነት ተፈረመ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 21/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የመረጃ፣ የቢዝነስና የመሰረተ ልማት ትብብር የሚያጠናክሩ ስምምነቶች ተፈረሙ። ስምምነቶቹ በሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ በሚገኘው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን አባላት የተፈረሙ ናቸው ተብሏል።
በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል አለም አቀፍ የመረጃ ደህንነትን በተመለከተ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ናቸው።
ስምምነቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የመረጃ ደህንነት ዘርፍ ላይ አቅምን ለመገንባት፤ የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ እንዲሁም የመሰረተ ልማትና የቴክኖሎጂ አቅምን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ነው።
የሁለቱን ሃገራት የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ማሳደግ ያለመው አንዱ ነው።
ስምምነቱን የፈረሙት የሩሲያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ኢጎር ቻሊክ ሩሲያ ከአፍሪካ ሃገራት ጋር ያላትን ትስስር ለማጠናከር የኢትዮጵያ አየርመንገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እና በሩሲያ የጉምሩክ አገልግሎት ሃላፊ ሩስላን ዳቪዶፍ መካከል የተፈረመው ስምምነትም በሁለቱ ሃገራት መካከል በዘርፉ ያለውን የክፍያና አገልግሎት ስርአት ለማዘመን የሚያስችል እንደሚሆን ተነግሯል።
በተጨማሪም ስምምነቱ የኢትዮጵያና የሩሲያን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያሰችል ነው።
More Stories
አካል ጉዳተኞች መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በቅንጅትና በጥምረት መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ
አካባቢን በመጠበቅና በማጽዳት ምቹና ጽዱ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ሁሉም የድርሻውን ልወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ
ግለሰባዊ ነጠላ ትርክቶችን በጋራ በመታገል በመደመር እሳቤ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ