በተጠናቀቀው በጀት አመት እንደሀገርም ሆነ ልዩ ወረዳ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለፀ

በተጠናቀቀው በጀት አመት እንደሀገርም ሆነ ልዩ ወረዳ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለፀ

ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 13ኛ አመት 35ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የቀቤና ልዩ ወረዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ፈቱዲን ሙዘሚል በዚህ ወቅት እንደገለፁት፤ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት አመት እንደሀገርም ሆነ ልዩ ወረዳ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋም ስኬታማ ተግባራት ማከናወን ተችሏል።

በ2018 በጀት አመት የልዩ ወረዳው ማህበረሰብ በልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠቃሚ ለማድረግ በየደረጃው ከሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በቅርበት ሲሰራ ቆይቷል ነው ያሉት፡፡

በተለይም ታሪካዊው ሀገራዊ ምክክር በስኬት መጠናቀቁ ኢትዮጵያ በልጆቿ መግባባት መፃኢ እድሎቿን በራሷ የመወሰን አቅም ማሳያ መሆኑንም አንስተዋል።

በሌላ በኩል ክልል አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በልዩ ወረዳው መደረጉን አስታውሰው፤ ይህም በውጤታማነት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ከማድረግና የስራ አፈፃፀምን በሪፖርት ከመገምገም ባሻገር የመስክ ምልከታ ሲያደርግ መቆየቱንም አክለዋል፡፡

በዚህም በተጠናቀቀው በጀት አመት በልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ማህበረሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸውን አውስተዋል፡፡

በቀጣይ የተስተዋሉ ውስንነቶችን በማረም በበጀት አመቱ የተያዙ ዋና ዋና ግቦችን ለማሳካት በሁሉም መስኮች ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ዋና አፈ ጉባኤው አስገንዝበዋል፡፡

ጉባኤው በተጠናቀቀው በጀት አመት በልዩ ወረዳው የተሰሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች በሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን የተጀመረ ሲሆን በቆይታውም የ2018 በጀት አመት አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የ2019 በጀት አመት ዕቅድ እና ረቂቅ በጀት ቀርቦ በመገምገም ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዘጋቢ፡ ሚፍታ ጀማል – ከወልቂጤ ጣቢያችን