በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ

በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 21/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ የሥራ መስኮች በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

በ2015 ዓ.ም የበጋ ወራት ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መዝጊያና የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ የ2015 የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ደም በመለገስ፣ በችግኝ ተከላ፣ ለአቅመ ደካሞች የቤት መስሪያ ቆርቆሮ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ዊልቸር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ደም በመለገስ የ2015 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ያስጀመሩት የወረዳው ዋና አስተዳደሪ አቶ በድሩ ሰንገሮ፥ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተሠሩ ሥራዎች የተለያዩ የአቅመ ደከማ ዜጎችን በመደገፍ ከችግር እንዲወጡ ያስቻለ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን መጀመር ብቻ ሳይሆን ለማጠናቀቅ ትኩረት መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፥ በየቀበሌ አቅመ ደከማ የሆኑ ወገኖቻችንን በመለየት በዚህ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር በፍትሃዊነት ማገልገል እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

የወረዳው  ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ይልማ፥ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመው፥ በዘንድሮ ክረምት በጤና፣ በግብርና፣ አቅመ ደካሞችን መደገፍ፣ መንገድ ጥገናና በመሳሳሉ ተግባራት ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ወጪ ለማዳን መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ: ሳጂዳ ሙደስር – ከሆሳዕና  ጣቢያችን