በሀገራችን ዘላቂ ሠላም ለማስፈን እና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር የጎላ ፋይዳ እንዳለው አንዳንድ የኮንሶ ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ
ሀገራዊ ምክክሩ ረጂም ዘመናትን የተሻገሩ ታሪካዊ እና ፖለቲካዊ ውዝግቦችን በውይይት ለመፍታት ብቸኛው ሠላማዊ መንገድ መሆኑን ከዞኑ ነዋሪዎች መካከል አባት ጡረተኛ አቶ ኮርባይዶ ጋንዶ ገልፀዋል፡፡
አባት ጡረተኛው አክለውም፤ ሂደቱ ሠላምንና የጋራ መግባባትን የሚያመጣ ታሪካዊ ዕድል ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ለዘመናት የቆዩ መሠረታዊና ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የተቋቋመው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ገለቦ ሽሎ ተናግረዋል፡፡
ልዩነቶች በውውይት ሊፈቱ ይገባል ያሉት አቶ ገለቦ፤ እየተካሄደ ያለውን ጉባኤ በአግባቡ መጠቀም የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ስለመሆኑም ነው ያስገነዘቡት፡፡
የዞኑ የሀገር ሽማግሌ አቶ ኩኒያ ቶራይቶ በበኩላቸዉ፤ በቀጣይ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ችግሮችን በዘላቂነት ማስወገድ፣ ጥላቻንና ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ሰላምን ማስፈን ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ኦላታ ኩስያ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገሩና መመካከሩ በሀገሪቱ ዘላቂ ሠላም ለማምጣት ምቹ አጋጣሚ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ: ተዋበች ዳዲ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የክልሉ ሕዝቦች ሰላምና አንድነት እንዲጎለብት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የብሔረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ገለጹ
ብሔራዊ መግባባት የሰፈነባትን ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ ሀገራዊ ምክክሩ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተገለጸ
የኮንታ ዞን ም/ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ ሥራ ዘመን 26ኛው መደበኛ ጉባኤው ተጠናቀቀ