የተቀናጀ መሬት አጠቃቀም ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግና የማኅበረሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በሳይንሳዊ ጥናት የታገዘ ተግባር እየተከናወነ ነው

‎የተቀናጀ መሬት አጠቃቀም ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግና የማኅበረሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በሳይንሳዊ ጥናት የታገዘ ተግባር እየተከናወነ ነው
‎
‎የተቀናጀ መሬት አጠቃቀም ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግና የማኅበረሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በሳይንሳዊ ጥናት የታገዘ ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ፎለር ኢትዮጵያ ፕሮጀክት አስታወቀ።
‎
‎በይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ፎለር ፕሮጀክት በተቀናጀ መሬት አጠቃቀም ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
‎
‎በውይይት መድረኩ በወረዳው በሚታየው የመሬት አጠቃቀም ተግዳሮትና መፍትሄ ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
‎
‎የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ድጋፌ ሙላቱ እንደገለጹት፤ መሬት ለትውልድ የሚተላለፍ ሃብት ስለሆነ አጠቃቀሙ በጥናት ላይ በተመሠረተ መልኩ መሆን አለበት።
‎
‎በወረዳው ያለው መሬት ከህዝብ ቁጥር ጋር ባልተጣጣመበት ሁኔታ ቀጣይነት ያለው ልማት ስለማይታሰብ መፍትሄ የሚጠቁም ጥናት እንደሆነ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ፎለር ኢትዮጵያ ፕሮጀክት አስተባበሪ አቶ አለምበጁ ክፍሌ ገልጸዋል።
‎
‎ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አርሶአደር ሽፈራዉ ተጫነ እና ኢያሱ ደያሶ፤ በሚያገኙት ግንዛቤ ምርታማነታቸው እየጨመረ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
‎
‎በመድረኩ የግብርና ምርታማነትን የሚያሻሽል የተቀናጀ የመሬት አያያዝና አስተዳደር ዕቅድ ቀርቦ ባለድርሻ አካላት የመግባቢያ ፊርማ ተፈራርመዋል።
‎
‎ዘጋቢ: አማኑኤል ትዕግሥቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን