የወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2019 በጀት ዓመት የሥራ ክንውን 1 ቢሊዮን 321 ሚሊዮን ብር በላይ በማጽደቅ ተጠናቋል

የወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2019 በጀት ዓመት የሥራ ክንውን 1 ቢሊዮን 321 ሚሊዮን ብር በላይ በማጽደቅ ተጠናቋል

የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሂዷል።

ጉባኤው በቀረበው የወረዳው አሰተዳደር ምክር ቤት የአስፈጻሚ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በማየት በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በጥልቀት መክሯል።

ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ አስተያየትና ጥያቄዎች የከተማው ከንቲባ አቶ ዘካርያስ ጃታ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ህዝቡን ያሳተፈ የልማት ሥራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ከንቲባው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የህዝቡ መሠረተ ልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ተሰርተው አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ጠቁመዋል።

በተለይም በጤና፣ ገቢዎች፣ በከተማው ግብርና፣ በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ከተማውን ለማዘመን በተጀመረው የኮሪደረ ልማት ሥራ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ነው ሲሉ አክለዋል።

በቀጣይም የህዝቡን አዳጊ ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የልማት ተግባራትን በማከናወን የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተመዘገቡ ስኬቶችን በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም በቀጣይም የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ተቀናጅተው ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ምክር ቤቱ ባደረገው 4ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2019 በጀት ዓመት የሚሆን ከ1 ቢሊዮን 321 ሚሊዮን 138 ብር በላይ በጀት በማጽደቅ ተጠናቋል።

ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን