የቤንች ሸኮ ዞን አሰ/ር ምክር ቤት የካቢኔ አባላት የ2015 በጀት ዓመት የአስፈፃሚ ተቋማት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በሚዛን አማን እያካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሚዛን አማን እየተካሄደ የሚገኘው የአስፈፃሚ ተቋማት የዕቅድ የአፈፃፀም ግምገማው ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።
በአፈፃፀም ግምገማው የተገኙት የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ቀበሌ መንገሻ እንደገለፁት በሀገር ደረጃ እየታየ ያለውን የኑሮ ውድነት እና የሥራ አጥነት ችግሮችን በዘላቂነት ለመቀርፍ እያንዳንዱ ተቋም የራሱን ተግባር በተደራጀና በተቀናጀ መምራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ተግባራቱን በየዘርፉ በመገመገም ለምክር ቤቶች ይቀርብ እንደነበረ አቶ ቀበሌ ገልፀው የአስፈፃሚ ተቋማት ተግባራት በተገቢው በመገመገም ለቀጣይ የ2016 በጀት ዓመት ጠቋሚ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዘበዋል።
የዞኑ አስተዳደር ምክር ቤት ካቢኔ የ2015 በጀት ዓመት የአስፈፃሚ ተቋማት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን የአስተዳደሩ ምክር ቤት የልማት ዕቅድ ባለሙያ በአቶ ትዕዛዙ አንታ እየቀረበ ይገኛል።
የዞኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማው የ 21 ሴክተር መስሪያ ቤቶች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በአስተዳደር ዘርፍ በቀድሞ መዋቅር የተደራጀ ሪፖርት መሆኑን ባለሙያው ተናገረዋል።
ግምገማው የዞኑ አስተዳደር የ2015 በጀት ዓመት የአስፈፃሚ ተቋማት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እንዲሁም የ2016 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድን በጥልቀት በመገመገም በቀጣይ ለምክር ቤት ጉባኤ በሚቀርብ ሁኔታ ምክክር ተደርጎበት እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
አካል ጉዳተኞች መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በቅንጅትና በጥምረት መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ
አካባቢን በመጠበቅና በማጽዳት ምቹና ጽዱ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ሁሉም የድርሻውን ልወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ
ግለሰባዊ ነጠላ ትርክቶችን በጋራ በመታገል በመደመር እሳቤ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ