የሰላም ሚኒስቴር እና የብሄራዊ ተሃዲሶ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች በጉራጌ ዞን ማረቆ ወረዳ የዘንድሮውን የክረምት በጎ ፈቃድ አግልግሎት አስጀመሩ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሰላም ሚኒስቴር እና የብሄራዊ ተሃዲሶ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች በጉራጌ ዞን ማረቆ ወረዳ የዘንድሮውን የክረምት በጎ ፈቃድ አግልግሎት በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል።
አመራሮችና ሠራተኞቹ “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ሀሳብ እንደ ሀገር እየተካሄደ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም የሚያጠናክር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አድርገዋል።
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንዳአ ከብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተወካይ አቶ ሻንቆ ደሳለኝ ጋር በመሆን 100 ለሚሆኑ የኢኮኖሚ አቅም ውስንነት ላለባቸው ቤተሰብ የተማሪዎች የትምህርት ግብአቶችን ድጋፍ ያበረከቱ ሲሆኑ ለ50 አረጋዊያን ደግሞ ጋቢ አልብሰዋል።
የአቅማ ደካሞችን ቤት ለማደስና የቆሼ ሽግግር የመጀመሪያ ደረጀ ትምህርት ቤት ለማስፋፋትም ቃል ገብተዋል።
የቤት እድሳቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቅቆ ለተጠቃሚዎቹ እንዲተላለፍ የቅርብ ክትልል እንደሚያደርጉም አመራሮቹ አረጋግጠዋል፡፡
የማረቆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ መኬ በበኩላቸው ከአዲስ አበባ 156 ኪሎ ሜትር ተጉዘው በመምጣት በወረዳው ላደረጉት በጎ ተግባር አመስግነዋል።
የሰላም ሚኒስቴርና የብሂራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ሠራተኞችና አመራሮች የተከሏቸው ችግኞች እንዲፀድቁ ተገቢውን የእንክብካቤና ጥበቃ ሥራዎች እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ
More Stories
ሳታ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ በአርባ ምንጭ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 132 ተማሪዎችን አስመረቀ
በዕቅድ የሚመራ የመፈፀም አቅሙ ያደገ ሲቪል ሰርቫንት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ገለፀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከውጭ ይገቡ የነበሩትን ሰብሎች በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሰራ ያለው ስራ ውጤታማ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰመስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው አስታወቁ