በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሠላማዊ ሁኔታ እየተሠጠ ነው
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከ6 ሺ 600 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና በሠላማዊ ሁኔታ እየወሰዱ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አለሙ ሀይላቴ ከተፈታኞቹ መካከል 89 የሚሆኑት ህፃን ይዘው የመጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
አንድ ነፍሰ ጡር ተማሪ በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል በሰላም የተገላገለች ሲሆን ፈተናውን በቀጣይ ዙር ትወስዳለች ተብሏል፡፡
የጂንካ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉድሼ ከፈተናው ጋር በተያያዘ ተቋሙ በቂ ዝግጅት አድርጎ ተማሪዎችን መቀበሉን አስታውቀዋል ።
እስከአሁን ድረስ ምንም ዓይነት ችግር አለመፈጠሩንም ተናግረዋል፡፡
ከትምህርት ሚኒስትር ፈተናውን ለማስተባበር ወደ ጂንካ ዩኒቨርስቲ የተመደቡት አቶ ፈቃዱ አሌ ከዘጠኝ ሺህ በላይ የተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ጂንካ ዩኒቨርስቲ ተመድበው የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየወሰዱ ይገኛሉ ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው ዝግጅት ጥሩ መሆኑንም ተመልክተናል ብለዋል አስተባባሪው፡፡
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ- ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ